Banner
yfÝDÂ MZgÆ                              QòC
yÞZB /ymNGST ÊD× fÝD
yÞZB /ymNGST t½l¤vþiN fÝD
y¥HbrsB ÊD× fÝD
    yWÀ yBéDµST PéG‰äCN tqBlÖ bKFà ldNb®C y¥DrS xgLGlÖT fÝD
    bygþz¤W y¸wÈ HTmT MZgÆ
*     *     *     *     *    *
bygþz¤W y¸nsù _Ãq½ãC
KMCT(Archive)
 
«Ý¸ DrgòC
xþÊt½D
êL¬
xþz¤x
xYtE†
xþK¬D
yBéDµStéC xD‰š
 
 
 yx¥R¾ ðd§T GDfT y¸ÃU_ä kçn update internet explorer 8

የብሮድካስት ባለስልጣን ሠራተኞች ቡና ጠጡ ሥነ ሥርዓት አካሄዱ””10-06-2003
  • በማሟያ ምርጫ እና ኤች አይ ቪ/ኤድስ ዙሪያ ተወያዩ

በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሴቶች ግብረ ኃይል ያዘጋጀው የግማሽ ቀን "የቡና ጠጡ - ቁም ነገር ተለዋወጡ" ፕሮግራም አርብ በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡

የባለስልጣኑ ሠራተኞች "ሴቶችና የማሟያ ምርጫ፣ ሴቶችና ኤች አይ ቪ/ኤድስ" በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የመነሻ ሀሳብ በምርጫ ቦርድ እና በሴቶች ግብረ ኃይል ባለሙያዎች ከቀረበ በኋላ ሞቅ ያለ ክርክርና ውይይት ያካሄዱ ሲሆን የዳቦ ቆረሳና የቡና መጠጣት ስነ ስርአት ተከናውኗል፡፡

ፕሮግራሙን አቶ ደስታ ተስፋው የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በንግግር የከፈቱ ሲሆን የማኀበረሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶች በእንደዚህ ዓይነቱ ማኀበራዊና ዴሞክራሲያዋ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ካልተሳተፉ አመርቂ ውጤት አይኖርም ብለዋል፡፡ ከዚህ አንፃር የሴቶች ግብረ ኃይል እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በአርአያነቱ የሚጠቀስ ነው፡፡ "ምርጫና ዴሞክራሲ ዲሞክራሲና ሴቶች - ሴቶችና ምርጫ የማይነጣጠሉና የተሰናሰሉ ናቸው" ያሉት አቶ ደስታ አያይዘው በምርጫና ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከምርጫ ቦርድ ጋር ተባብሮ ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ይስማው ጂሩ በበኩላቸው "በምርጫ አይነቶች፣ በምርጫ አሰፈላጊነት፣ በምርጫና በሴቶች ሚና" ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ ሰጥተዋል፡፡ የካቲት 20 ቀን 2003 ዓ.ም. በሚካሄደው የማሟያ ምርጫ ላይ የባለስልጣኑ ሠራተኞች ከውዲሁ ተመዝግበው በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀረቡት የምርጫ ቦርድ ባለሙያ በሀገራችን አምስት የምርጫ ዓይነትቶች መኖራቸውንም አክለው ገልፀዋል፡፡

አቶ ይስማው ጅሩ የማሟያ ምርጫን አስመልክተው ለባለሥልጣኑ ባለሙያወች ገለጻ ሲያደርጉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት በተለያየ ምክንያት የጎደሉ የምክር ቤት አባላትን እንዲሟሉ የሚያደርገውን የዘንድሮ የማሟያ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጀት ማጠናቀቁን አብስረዋል፡፡

የባለስልጣኑ ሠራተኞች በበኩላቸው ልዩ ልዩ ወቅታዊ ጥያቄዎችን ለባለሙያው ያቀረቡ ሲሆን በቂ ምላሽና ማብራሪያም አግኝተዋል፡፡

ወ/ሪት መታገስ ሳሙኤል የብሮድካስት ሚዲያ ክትትልና ድጋፍ ቡድን አባልና የሴቶች ግብረ ኃይል አባል "ሰው ለሰው" የሚል መጣጥፍ በመንደርደርያነት በማቅረብ በኤች አይ ቪ/ኤድስ እና በስርዓተ ፆታ ዙሪያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ትምህርት የሰጡ ሲሆን ሴቶች ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ በሆኑ መንስኤዎች ከወንዶች በበለጠ ሁኔታ ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው ብለዋል፡፡ የሴቶች ጉዳይ ደግሞ የወንዶችም ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም በያገባናል ስሜት በስርአተ ፆታና ኤች አይ ቪ/ኤድስ ዙሪያ በንቃት መሳተፍና ለውጥ ማምጣት ይገባናል ብለዋል፡፡

በግልፅ መነጋገር፣ መወያየት፣ መረዳዳትና መተጋገዝ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ችግሮቻችን መፍቻ ቁልፎች ማጠንጠኛ መዘውር ነው የውይይቱ መሪ መልዕክት ነበር፡፡

አቶ ሙሉጌታ ሲሳይ የሠው ሀብት አመራርና ልማት የሥራ ሂደት ዳይሬክተር ፕሮግራሙን ሲዘጉ ሠራተኛው ከውይይቱ በቂ ግንዛቤ መጨበጡን ሆኖም ይህ ብቻ በቂ አለመሆኑና በተግባር መተርጎም እንዳለበት ገልፀው ሠራተኛው ይህን መሰሉን መድረክ ካዘጋጀው ግብረ ኃይል ጋር ወደፊትም መቆምና መደገፍ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

Updated September 2009 Copyright © 2009
Ethiopian Broadcasting Authority. All righs reserved.
You Are Visitor Number
website hit counter


ENGLISH PAGE
   
               
Bé¹R
¥HbrsB ÊÄ× BéDµST xgLGlÖT
fÝD ywsÇ y¥HbrsB ÊÄþü BéDµST xgLGlÖT ÈBÃãC ZRZR mr©
Sl mS¶Ã b¤tÜ x«Ý§Y mr©
QʬãC _ö¥ãC
z¤Â mIÿT
xm¬êE mI¼¤T
PÊS ¶lþZ
æè Ul¶